Home

እንኳን ለ2013 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!!!

እንሆ እንደተለመደው በዚህ ዓመትም በ15.08.2020  የሕይወት መዕራፍን አንድ ብለው ለሚጀምሩ ልጆቻችን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የኢትዮ- በርሊን ማህበር አባላት እንዲሁም የሕጻናቱ ቤተሰቦች  በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል ” ቤተሰቦቻችሁን የምታኮሩ ሀገራችሁን የምታስጠሩ መልካም ዜጋ ” እንደምትሆኑ አምላክ ይርዳቺሁ እያልን መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን !!!

በኢትዮ – በርሊን ማህበር የተዘጋጀው በበርሊን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን “እኔም ለዓባይ አለሁ” በሚል በተለይም ታዳጊ ሕጻናት እኛም አሻራችንን ማስቀመጥ አለብን በማለት የተሳተፉበት እንዲሁም በታዋቂዋ ሠዓሊ በየናትፋንታ አባተ የተበረከተ ሥዕል ለጨረታ ቀርቦ ከፍተኛ ገቢ የተገኘበት የገቢ ማሰባሰሰቢያ ፕሮግራም 01/08/2020 በርሊን

ቅዳሜ July 18 የጀርመን ከተሞች ደማማቅ ሰልፎች ተደረጉ።
====================
የጀርመኗ ዋና ከተማ በርሊን፣ የሀበሻ መናኸሪያዋ ፍራንክፈርት እና የኑረንበርግ ከተማ በተመሳሳይ ቀን እና ሰዐት ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገውባቸዋል። በሁሉም ከተሞች ኢትዮጵያዊነት ነግሶ፣ አንድነታችን አይሎ ታይቷል ስንተባበር እና አንድ ስንሆን ጠላቶቻችንን ምን ያህል አንገት የምናስደፋ መሆናችንንም አሳይተንበታል። ኢትዮጵያ አትፈርስም ሊያፈርሷት ያሰቡት ግን ይወድቃሉ።

በጀርመን ዋና ከተማ በበርሊን እና በአካባቢዋ በሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እና ትውልደ ኢትዮጲያውያን 124ኛውን የአድዋ የድል ቀን በአል እ.ኤ.አ  ማርች 7. 2020  በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

 • ኢትዮበርሊን አደዋ ክበረበአል 07.03.2020

ሶስቱንም ማእዘናት የተመለከተ ነጻ ውይይት በበርሊን!!

ማህበራችን ኢትዮ በርሊን በአይነቱ ልዩ የሆነ ስለ ወቅታዊ የሀገራችን ፖለቲካ ሁኔታ ውይይት ፌብርዋሪ 15/ 2020 ዓም አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ ዝግጅት ላይ ታዋቂው ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ አናንያ ሶሪ ያለውን ልምድ እንደ መነሻ አቅርቦ ነበር። ከእሱም በተጨመማሪ ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠር ያለ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተወያዩ እንደ መነሻ እንዲወስደው አድርጓል ። በስብሰባው ላይ ከበርሊንና አካባቢዋ የመጡ ኢትዮጵያውያን ሞቅ ያለ ተሳትፎ አድርገዋል። የውይይቱ አካሄድ ከዚህ በፊት ከተለመደው ለየት ባለ ሁኔታ ሶስቱን ማእዘናት ማለትም ያሉትን ወቅታዊ ጥሩ አጋጣሚዎች፣ አደገኛ የሆኑ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታዎችንና መፍትሄዎቻቸውን የተመለከተ ነበር።
ከብዙ በጥቂቱ ከመድረኩም ይሁን ከተሰብሳቢው የሚከተሉት ነጥቦች ተሰንዝረዋል። የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት፣ በውጭ አገር በስደት የነበሩ የተወሰኑት ፖለቲከኞች ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው፣ የህዝቡ ንቃተ ህሊና መጨመርና የመሳሰሉት እንደ ወቅታዊ አበረታች ሁኔታዎች ሲታዩ፣ የህገ ወጥነት መስፋፋት፣ የህግ የበላይነት አለመከበር፣ ጎሰኝነት፣ የአንድነቱ ኃይል መዳከም፣ የአድነት ኃይል ደጋፊው ከፍተኛ የሆነ የጠባቂነት ስሜት ፣ የውጭ አገር ሚዲያዎችና የሰብአዊነት ድርጅቶች አድሎአዊነትና የመሳሰሉት እጅግ አደገኛ የፖለቲካ ሁኔታዎችን በዚህ ወቅት እንደተፈጠሩ ተወያዮቹ ጠቅሰዋቸዋል።
እንደ መፍትሄ ከተቀመጡት ነጥቦች ውስጥ ከአጉል ተስፈኝነትና ጠባቢቦቂነት በመውጣት በሀገር ውስጥ ያለውም ሆነ በዲያስፖራ ያለው ኢትዮጵያዊ እንደገና በመደራጀት የሀገርን ህልውና ማስጠበቅ፣ የተዳከመውን የአንድነት ኃይል በተቻለው ሁሉ በማጠናከር ተገዳዳሪ የፖለቲካ ኃይል እንዲሆን መርዳት፣ ልዩነትን ማጥበብ፣ ጀርመን አቀፍም ሆነ አውሮፖ አቀፍ የዲያስፖራ ድርጅቶችን ማዋቀር፣ የዚህ አይነት ውይይቶችን በመላው አውሮፖ እንዲጠናከሩ ማገዝ፣ በሀገር ቤት እየተደረጉ ያሉትን ጉዳዮች በአካል አጥንተው ሪፖርት የሚያደርጉ ቡድኖችን ማዋቀር፣ በሀገር ውስጥ እየተደረጉ ያሉትን አደገኛ ሁኔታዎች ለሚመለከታቸው አለም አቀፍም ይሁን አገር አቀፍ ተቋማት ማሳወቅ፣ የማብራሪያ ደብዳቤዎች ለኢትዮጵያ ኤምባሲ መጻፍና የመሳሰሉትን እንደ መፍትሄ ተቀምጠዋል።
ውይይቱ እጅግ ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ከቀኑ 15:30 ተጀምሮ ከምሽቱ 18:30 ተጠናቋል። በቀጣይም ተመሳሳይ ዝግጅቶች እንዲደረግ ም መግባባት ላይ ተደርሷል።
ሁላችንም የበኩላችንን ብንወጣ ለችግራችን መፍትሄ በእጃችን ላይ ነው!!
ኢትዮ በርሊን ማህበር

በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሰላማዊ ሰልፍ በርሊን

በጀርመን :የኢትዮጵያ እርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፅህፈት ቤት በርሊን ላይ በጠራው ሰላማዊ ስልፍ ክጠቅላላው የጀርመን ከተሞች በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በመገኘት :ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል ::በሰልፉ ላይ ካስተላልፉት መልእክቶች ውስጥ –በከፊል የመንግስት ቸለተኝነት ይብቃ: የንፁሀን ደም መንግስትን ሊያሳስበው ይገባል : ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ : አብያተ ክርስትያናትን በማቃጠል የኦርቶዶስ ተዋህዶን ማጥፋት አይቻልም …………….የመሳሰሉና ሌሎች በርካታ መልእክቶችን አስተላልፈዋል !!!

Auf weltweitem Aufruf der äthiopischen orthodoxen Kirche gegen die Gräueltaten an die äthiopische Kirche und ihre Gläubiger zu protestieren, fand am 06.12.2019 in Berlin eine große Demonstration statt. Im Laufe der letzten 6 Monate wurden in Äthiopien über 10 Kirchen in Brand gesetzt, viele Priester und zahlreiche Gläubiger der äthiopischen orthodoxen Kirche auf brutaler Weise umgebracht.

Die Demonstration hat das Ziel, die deutsche Öffentlichkeit darüber zu informieren, und die Aufmerksamkeit der deutschen Regierung zu wecken.An dieser mit äthiopischen Fahnen geschmückten und mit Kirchengesang begleiteten Demonstration  haben sehr viele aus verschiedenen Bundesländern eingereiste Äthiopier zusammen mit ihren Familienangehörigen und zahlreichen deutschen Freunden teilgenommen.

Nach der Übergabe der schriftlichen Petition beim Bundeskanzleramt wurde sie im weiteren Verlauf  auf Amharisch und  Deutsch  den Demonstranten verlesen.Zum Schluss dankte Kesis Melake Mewie Lisanework den trotz des schlechten Wetters zahlreich erschienenen Teilnehmern  und hielt eine kleine Messe ab, um den Verstorbenen zu gedenken und für sie zu beten.

Anschließend bedankte sich Herr Belayneh im Namen der Kirche in Berlin bei den Demonstranten, begleitenden  Polizisten  und erklärte die Demonstration für beendet. Hier einige Plakate, mit denen die Demonstranten ihre Anliegen und Forderungen zum Ausdruck brachten wie folgt:

Die äthiopische orthodoxe Kirche ist die einzige christliche Kirche der Welt mit eigener Sprache und Schrift (Geez) , die als  Weltkulturerbe  von der ganzen Welt geschützt werden muss.

የኢትዮበርሊን ማህበር ያባላቶች ቀን

 • ኢትዮበርሊን መህበር ያባላቶቸ ቀን

አንኳን ለ2012 አመተ ምህረት በሰላም አደረሳችሁ!!!

በበርሊን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን 2012 አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ በኢትዮበርሊን ማህበር አዘጋጅነት አ.አ.አ በ14.09.2109 በታላቅ ድምቀት ተክብሮ ዋለ!!!

 • ኢትዮበርሊን 2019

 

 

በበርሊን ከተማ በኢትዮበርሊን ማህበር አዘጋጅነት በየመቱ የሚከበረው አዲስ የትምህርት አለም ለሚጀምሩ ህጻናት የተዘጋጀው ፕሮግራም በታላቅ ድምቀት ተከበሮ ውሏል፡፡

በ 22.06.2019 በአትዮበርሊን መህበር የተዘጋጀው ግሪልፓርቲ ቴምፕልሆፍ በሚገኘው የሰርከስ ቅጥር ግቢ የተሳካና አዝናኝ ነበር!

 • Grillparty 22.06.2019 Berlin Tempelhof, Ethioberlinev

 

 

Victory celebration in Berlin with

      Dr. Prince Asfawossen and Dr. Fekadu Bekele

**************************************************************************************************************

On the occasion of the 78 th anniversery of the victory of the Ethiopian people against the fashist Italian occupation army, was celebrated colourfully in Berlin on Saturday 4/5/2019.

The celebration was organized by the Ethio-Berlin Verein e.V… (association of Ethiopian origin diaspora in Berlin)

High officals of Federal German Ministry of Affairs, Ethiopian Embassy members, Members of Chameber of Commerce in Berlin, Professors from Freie Universitaet Berlin, members of the Heinrich Boell Foundation organization, German Private sector Investors and Ethiopian diaspora and friends of Ethiopia have attended the colourful ceremoney.

Guest of Honered Dr. Prince  Asfawossen, best seller author and consultant adviser, political analyst- held the opening speech, which was followed by panel discussion on current Ethiopian political situation. Patiotic songs was presented by Ethio-Berlin youth and Ethiopian cusine was served during the overwhelming successful celebration!

የ123ኛው የአደዋ በአል በበርሊን ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ

ትናንት 123ኛውን የአድዋ በአልን ለማክበር ማህበራችን በተነሳበት ወቅት የተነሳባቸውን መሰረታዊ ግቦች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ አሳክቷል። ለዚህ ውጤት ሁላችሁም አስተዋጾ በማድረጋችሁ እጅግ የሚያኮራ ነበር። ከዚህ ስኬት የተረዳነው በውስጣችን የታመቀ ኃይል መኖሩን ነው።
ሴት እህቶቻችን በቲያትሩ፣ በምግብ ዝግጅቱ፣ በስነጽሁፉ፣ በዝግጅት ኮሚቴነት ወዘተ በተመደቡበት ኃላፊነት ሁሉ በብቃት እንደ አንድ ሰው መወጣታቸው የሚደነቅ ነበር። ሌሎች ንኡሳን ኮሚቴዎችም እንዲሁ በቅንጅት አመርቂ ስራ ሰርተዋል።
ታዳሚው በብዛት፣ አዳራሹ እስኪሞላ ድረስ በሰአቱ እጅግ ኢትዬጵያዊ ጨዋነት በተሞላበት ማሳለፉ ይበልጥ እንድንሰራ አበረታቶናል።
የማህበሩ ግብ ይበልጥ እንድንቀራረብና የተሻለ ስራ ለሀገራችን እንድንሰራና ልጆቻችን የኛን ፈለግ ተከትለው የበለጠ እንዲሰሩ ለማድረግ ነው።
ከተባበርን የማናሸንፈው ችግር የለም!!
የኢትዬ በርሊን ማህበር

 

 

   ዜና ኢትዬ በርሊን

መቀመጫውን በበሊን ከተማ ያደረገው የኢትዬ በርሊን የኢትዬጵያውያን የሲቪክ ማህበር ትናንት በፌብሩዋሪ 2. 2019 ዓ ም የተመሰረተበትን 5 ኛ አመት በአልና የስራ አመራር ምርጫ አካሂዷል።
ማህበሩ የሚከተሉትን መሰረታዊ አላማዎች አንግቦ የተቋቋመ ድርጅት ነው
*  ሁሉንም ኢትዬጵዬዊ በእኩልነት የሚመለከት፣
*  ባህላዊና እስፖርታዊ ዝግጅቶችን በማካሄድ የማህበረሰብ ቅርርብ መፍጠር፣
*  ለልጆች፣ ለወጣቶች፣ ለሴቶች ገንቢና አስተማሪ የሆኑ ዝግጅቶችን ማዘጋጀት
*  ትምህርታዊ የሆኑ ውይይቶችን ማዘጋጀት
እና የመሳሰሉት ናቸው ። እጅግ ብዙ ፈታኝ ዘመናትን አባላቱ አሳልፈዋል። ከነዚህም ውስጥ የኢትዬጵያውያን በማህበር በአንድ አላማ የመጓዝ ልምድ አለመኖር፣ የሰው ሀይልና የቁሳቁስ እጥረት፣ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች፣ በሀገር ቤት የነበረው አፋኝ መንግስት በዲያስፖራ ወኪሎች አማካኝነት የማፍረስ ዘመቻ፣ የመሳሰሉት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።
ማህበሩ በትናንትናው እለት ፍጹም ዲሞክራሲያዊ በሆነ የምርጫ ስልት የስራ አስፈጻሚ ምርጫ አካሂዷል። በመጀምሪያ ለያንዳንዱ መራጭ ምርጫ የሚያደርግበት ካርድ የታደለ ሲሆን መራጮችም የሚፈልጉትን ተመራጭ ስም በመጻፍ ለቆጣሪዎች በመስጠት በህዝብ ፊት እንዲቆጠር ተደርጓል። በዚህም መሰረት አቶ ታደሰ ቶላ ሊቀመንበር፣ አቶ መሳይ አበበ ም/ ሊቀ መንበር፣ አቶ ዳዊት ሳሙኤል ዋና ጸሀፊ፣ አቶ ወሰኑ ፈይሳ ገንዘብ ያዥ፣ አቶ ጋሻውን አባል በማድረግና አቶ አድማሱንና አቶ ተበጀን ኦዲት በማድረግ ተመርጠዋል።
በበአሉ ወቅት የነበረው የስራ አስፈጻሚ የስራ ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን ከተሰብሳቢውም የተለያዩ ገንቢ አስተያዬቶች ተሰጥተዋል። በዝግጅቱ ላይ ወላጆች ከነ ልጆቻቸው፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የማህብሩ አባላት፣ አዲስ ወደ ማህበሩ ለመመዝገብ የመጡ ኢትዬጵያውያንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዚህ አጋጣሚም ማህበሩ የተነሳበትን አላማ ግቡን እንዲመታ የሁሉም ኢትዬጵያዊ ጥረት ስለሚያስፈልገው ከጎኑ እንድትቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን።
እጅ ለእጅ ተያይዘን ለውጥ እናመጣለን!!

 

በጠቅላይ ሚኒሰትር ዶክተር አብይ አህመድ ባቀረቡት ” በጋራ ኢትዮጵያን የመገንባት (Working together to build a better Ethiopia)” በሚል ጥሪ በዉጭ የሚኖረው ኢትዮጲያዊና ትውልደ ኢትዮጲያዊ አቅርበዋል፡፡ ይህንን ጥሪ በመቀበል ታዋቂ በሆኑ የቦርድ ስብሳቢዎች ድህረገጽ ተሰርቶ እርዳታውን ማሰባሰብ በመላው አለም ተጀምሯል፡፡ ይህንን ጥሪ በመደገፍ የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ የምንፈልግ ሁሉ ከዚህ በታች በሚጠቀሰው ድህረገጽ እየገባችሁ ተጨማሪ ማብራሪያ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

ethiopiatrustfund  ⇒       https://www.ethiopiatrustfund.org/

Ethio-Berlin ኢትዮበርሊን e.V.Barbarossa Str. 65 – 10781 Berlin

ቀን 12.11.18
ቁጥር12112018/17

ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ

በርሊን

ጉዳዩ፣ በኦክቶበር 31 ቀን 2018 ዓ ም በዶ/ር አብይ አቀባበል ወቅት ስለተፈፀሙ ያልተገቡ ድርጊቶች ማብራሬያ ስለመጠየቅ።

እንደሚታወቀው ማህበራች ኢትዬ በርሊን በበርሊንና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዬጵያውያንን ለማገልገል የተቋቋመ ሲቪል ማህበር ነው። ማህበራችንም አባላቱን በማሳተፍ ላለፉት በርካታ አመታት በሀገራችን ጉዳዬች በንቃት ይሳተፋል። የማህበራችን አባላትም ይሁኑ ሌሎች በርካታ ኢትዮጰያውያን ላለፉት 27 አመታት አምባገኑንና ከፋፋዩን የወያኔ አገዛዝ አንድ ቀን ሳያቋርጡ ሲቃዎሙት እንደነበረና በርሊን በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር አሉታዊ ግንኙነት እንደነበረን ይታወቃል። ነገር ግን ባለፉት 6 ወራት በተፈጠረዉ የለዉጥ ሂደቶች እና ጠቅላይ ሚኒስተራችን ባደረጉት የመደመር ጥሪ ማህበራችን በግንባር ቀደምትነት ሀሳቡን በመደገፍ ሀላፊነት በመውሰድ መላው የበርሊን ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በታደሙበት በ28/07/2018 ዓ ም የመደመር ዝግጅታችን ላይ የኢምባሲዉ ተወካይ እንዲገኝልኝ በቀን 20/07/2018 ዓ ም በቁጥር 2018/02 ደብዳቤ ፅፈን በዝግጅቱ ላይ እንድትገኙልን አድርገን ነበር::

ይህንንም ሰላማዊ ግንኙነት ተከትሎ ኤምባሲው ባደርገልን ጥሪ መሰረት የማህበራችን ስራ አመራሮች በኤምባሲው ግቢ በመምጣት ግንኙነታችንን የበለጠ መተማመን እንዲኖርበት ተደርጓል:: ከላይ በርዕሱ ወደጠቀስነው ጉዳይ ስንመጣ ዶ/ር አብይን በፍራንክፈርት ለመቀበል በሚደረገው ዝግጅት ወቅት ከማህበራችን ተወካዮች ተመርጠው በንቃት ለዝግጅቱ መሳካት በቅን ልቦና እስከ መጨረሻው ሲያገለግሉ ነበር:: ነገር ግን በመጨረሻው ሰአት እጅግ ሸፍጥ በተሞላበትና ከአንድ አገርን ከሚወክል ተቋም በማይጠበቅ መልኩ ከዚህ በታች የዘርዘርናቸዉ ድርጊቶች ተፈፅመዋል፣

 1. በስምምነታችን መሰረት 7 ንኡሳን ኮሚቴዎች ተመርጠው የተለያየ የስራ ዘርፍ ተሰጥቶን ከአንድ ወር በላይ በቅንነት ስናገለግል ቆይተንና በዝግጅቱ ወቅት በጥዋት ተገኙ ተብለን ቀድመን ተገኝተን ያለምንም ስራ እንድንውልና ወደ መድረክ እንዳንገባ መደረጋችን:: በተጨማሪም ቀድሞ ወደ መድረክ እንድንገባበት የተሰጠን የመግቢያ ባጅ በእለቱ እዚያ ስንደርስ ህገ ወጥ የሆነና የተሰረዘ መሆኑ።
 2. በስምምነታችን መሰረት ጥያቄ ለዶ/ር አብይ ለማቀረብ በፅሁፍ አቅርቡ ተብለን ለምን ጥያቄአችን እንዳይቀርብ ተደረገ?
 3. በርሊን ነዋሪ ኢትዮጵያውያንን በመወከል እኛን ጨምሮ 4 ተወካዮች የነበሩ ሲሆን መድረክ ላይ ወጥቶ እንዲናገር የተፈቀደው አንድን ማህበረሳብ የሚወክል ብቻ እንዲቀርብ የተደረገዉ በምን መስፈርት ነበር?
 4. ወደ እስታዲየሙ በምንገባበት ወቅት የተወሰኑትን አባሎቻችንን ጥንታዊውን የአባቶቻችን መስዋእትነት የከፈሉበትን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማ እንዳይገባ የተከለከለበትን ምክንያት? በአንጻሩ ደግሞ በር ላይ ለነበሩት የጥበቃ ሰራተኞች የአንድ ድርጅት አርማ (ባንዲራ) ብቻ እንዲያስገቡ መደረጉ።

ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ እጅግ በርካታ ጥፋቶች ቢኖሩም ማህበራችንን በቀጥታ የሚመለከቱትን ብቻ ዘርዝረናቸዋል። ስለዚህ እኛ ደረጃውን ጠብቀን እስከ ላይኛው የስልጣን ተዋረድ ይህን ሴራ በኛም ይሁን በዝግጅቱ ላይ የፈፀሙት ተገቢዉን ቅጣት እንዲያገኙ ትግላችንን የምንቀጥል ሲሆን ቢሮዎት ለጉዳዩ አፅንዎት ሰቶ ተገቢዉን ማብራሪያ ይሰጠን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን::

ከሰላምታ ጋር!!

ግልባጭ:-

ለኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ለኢቢሲ ቴሌቪዥን

ለኢሳት ሬድዬና ቴሌቪዥን


በበርሊን ጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የድጋፍ አቀባበል እያደረጉ ነው።

በበርሊን ጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የድጋፍ አቀባበል እያደረጉ ነው።

Gepostet von ESAT am Dienstag, 30. Oktober 2018

Gepostet von Abyssinia ኢትዮጵያ ሬድዮ am Sonntag, 7. Oktober 2018

ኢትዮበርሊን ማህበር  ከ 2010 ወደ 2011 ዓ.ም እንኳን በሰላም አደረሳችሁ

እያለ መጪው አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና ፣የፍቅርና የመደመር አመት

እንዲሆንላችሁ ይመኝላችሗል!!! አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ

የኢትዮበርሊን ማህበር  በበርሊን ከተማ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ

ኢትዮጵያውያን ጋር በታላቅ ድምቀት አክብረነዋል፡፡

 

 

Ethioberlin e.V. Eingschulung in Berlin !!!

❤️❤️❤️❤️ # እንደተለመደው እና ሁልግዜም እንደምናደርገው :የ2018 ትምህርት ጀማሪ ልጆቻችንን :ቀን በተሳካ ሁኔታ አክብረናል :ይህ በየአመቱ በኢትዮ በርሊን የሴቶችና የህፃናት ንኡስ ኮሚቴ የሚዘጋጀው የትምህርት ጀማሪዎች ቀን ያማረና የደመቀ እንዲሁም በልጆቻችን ላይ ፍፁም ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮኢትይጵያዊ ስነምግባር እንዲሰርፅ ባለን የፅና አቋም :የሴቶችና የህፃናት ንኡስ ኮሚቴያችን ጠንክረው እየሰሩ እንደሆነ ያሳዩበት :መሆኑን አይተናል :ለዚህም በኢትዮ በርሊን የስራ አመራር ስም እና በመላው የማህበራችን አብላቶች ስም ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ 🌹 መጪው አመት :መልካም የትምህርት ዘመን ለልጆቻችን እንዲሆን እንመኛለን ## wir wünschen euch einen wundervollen Schulanfang ❤️ !Ethio Berlin .እ/ር ኢትዮጵይይን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ !!!!

 • Einschulung 2018 Berlin

 

የኢትዮበርሊን ማህበር ለአገራችን ሰላም እና ፍቅር ጎህ ቀዳጅ ለሆኑት አዲሱን የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የለውጡ አጋሮቻቸውን በበርሊን የሚኖሩ ኢትዮጲያኖች እና ኢርቲሪያኖች ድጋፋቸውን ሰጡ!

https://www.facebook.com/mayazenye415/videos/1383569405120161/

በርሊን ተደምረን አደማመርን..

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እይታ በመከተል፣ ተደምረን አደማመርን.. የኢትዮጵይ ኤምባሲ አባላትና የኤርትራ ወንድም እህቶቻችን እንዲሁም የኤርትራ ኮምዩኒቲ ሃላፊዎች በበዐሉ በመገኘት በጣም ደስ የሚልና ለፍቅር የሚበጅ ጊዜን ለማሳለፍ ችለናል… በቅድሚያ በዓሉን በኢትዮ-በርሊን ሊቀ መንበር አቶ ታደሰ ቶላ ከተከፈተ በሗላ፤ በዶር ፈቃዱ በቀለ፣ በአቶ ሃይሌ መንገሻ፣ በኤርትራ ኮሚኒቲ ተጠሪ፣ እና በኢትዮጵያ ኤምባሲ አባላት ገንቢ ንግግሮችንና እንዲሁም ድርሰቶች ተሰምተዋል.. በተረፈ እጅግ በጣም ደስ የሚል ስሜታዊ ዕለት ነበር… ከአብያችን ጋር ወደፊት…********************************************ቪዲዎ ቅጂና አርትዖት የተደረገው በግዛው መሸሻHome video made and edited by Gizaw Meshesha

Gepostet von Gizaw Meshesha am Sonntag, 29. Juli 2018

 

የኢትዮበርሊን ማህበር ለአገራችን ሰላም እና ፍቅር ጎህ ቀዳጅ ለሆኑት አዲሱን የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የለውጡ አጋሮቻቸውን ድጋፍ ለመስጠት ይህን ዝግጅት አዘጋጅተናል!!!

Solidaritäts-Bazar mit dem Reformkurs des äthiopischen Premierministers Dr. Abiy Ahemed

የአገራችንን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከኢትዮበርሊን ማህበር የተሰጠ መግለጫ

                          

 

Ethioberlin e.V.

c/o Kiezoase

Barbarossa Str. 65

10781 Berlin

Email: info@ethioberlinev.com

http://www.ethioberlinev.com

Tel.:+491712881417

 

እኛ  በበርሊን  የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ  ኢትዮጵያውያን ፣ ባለፉት 27 አመታት የሀገራችንን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን  እየተከታተልን ፣ በሀገራችን ይፈጸም የነበረውን  የመብት ረገጣ በመቃወም ፣ ከህዝባችን ጋር በመቆም ፣ ድምፅ ለሌላቸው ወገኖቻችን ድምፅ  በመሆንና  ፣ በተለይም በምንኖርበት አገር  የሚገኘውን የጀርመን መንግስትንና ፓርላማውን የአገራችንን ሁኔታ  በማሳወቅና ለህዝቡ የዲሞክራሲ ትግል  እገዛ እንዲያደርጉ በመጎትጎት ፣ በኢትዬጵያ  ዲያስፖራነታችን  የሚያስፈልገውን  ሀገራዊ ግዴታ ስንወጣ ቆይተናል ።

ነገር ግን በአሁኑ ሰአት  በሀገራችን  ውስጥ  ፣ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይና  ቡድናቸው አማካይነት በጣም ፈጣን የሆነ  የዲሞክራሲያዊ ለውጥ እየተተገበረ  በመሆኑ  የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ  አግኝቷል  ።ከ20 ሺ በላይ የፖለቲካ እስረኛ  በማስፈታትና   ፣ የሃሳብና የሚድያ ነፃነትን በመፍቀድ ፣ ህዝቡን ነፃነት በማጎናፀፍ ላይ ይገኛል።

ስለዚህ እኛ በበርሊን የምንገኝ ኢትዮጵያኖች ፣ ለዚህ በዶ /ር አብይ ለተጀመረው  የለውጥ እንቅስቃሴ ያለንን አድናቆትና ድጋፍ በዚህ  አጭር የአቋም መግለጫ ለመግለፅ  እንፈልጋለን ።

ይኸንን አቋማችንን ለምንወደውና ለምናከብረው  ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲተላለፍልን  ፣ እየጠየቅን  ከወገንተኝነት የፀዳ ሁሉን ኢትዮጵያዊ እኩል የሚመለከት  ዲሞክራሲያዊ ስርአት  እስከሚረጋገጥ  ወንጀለኞች ለፍርድ እስከሚቀርቡ ድረስ ትግላችንን እና ድጋፋችንን ባለንበት  አገር እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን።

በተጨማሪም በምንኖርበት አገር የሚገኘውን የጀርመን መንግስትና  የአውሮፓ ፓርላማ  ተጠሪዎች  ፣ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የህዝቡን የለውጥ እንቅስቃሴና  የዶ/ር አቢይን  መንግስት እንዲደግፉት ፣ በለመድነው መንገድ የፓርላማ አባላትን በማነጋገርና  ሰለማዊ  ሰልፍ በማድረግ ለማሳወቅ ያላሰለሰ ጥረት እንደምናደርግ  ቃል እንገባለን  ።

እንደነዚህ አይነት በአፍሪካ  ዴሞክራሲያዊ ለውጦች  የሚከተሉ መንግስታትን መደገፍ   ጠቃሚነት እንዳለው እንገልፅላቸዋለን።

ሌሎች  የዲያስፖራ  አባላት  እንደዚሁ ለዶ/ር  አቢይ ድጋፍ ቢሰጡ ፣ ላለበት ከአክራሪ የወያኔና የሌሎች  የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ጋር ለሚያደርገው  የሞት የሽረት ትግል የሚያግዘው ስለሆነ  ቢታሰብበት ጥሩ ነው እንላለን ።እስካሁን በተገቢው ሁኔታ ስራ ላይ የዋለው  የዲያስፖራው   የውጭ ምንዛሪ ሀዋላ ክልከላ መነሳቱን የምንደግፍ ሲሆን የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ የተሻለ እንዲሆን አባላቶቻችን እና ደጋፊወቻችን በህጋዊ ባንኮች እንዲጠቀሙ እንመክራለን ፣ መንግስትንም እንደእስካሁኑ ለዜጎች ማፈኛ ሳይሆን ላገር ልማት እንዲያውል እናሳስባለን። በመጨረሻም በቅርቡ በአዲስ አበባ እርስዎን ለመግደል ሙከራ ያደረጉትን አሸባሪዎች በጽኑ እያወገዝን በአሶሳ፣በሀዋሳ፣ በምስራቅ ሀረርጌ እና በሌሎችም ቦታዎች ደም ያፈሰሱ ወንጀለኞች  በፍጥነት ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

ኢትዬጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!!

የኢትዬ. በርሊን የሲቢክ ማህበር አባላትና ደጋፊዎች።

ሰኔ 3.2010 አ.ም.

በርሊን

እ.አ.አ 07.07.2018 በኢትዮበርሊን ተደርጎ የነበርው የ ግሪል ፓርቲ ይህን ይመስል ነበር!

 

https://www.facebook.com/mayazenye415/videos/1358645964279172/

ይህን ተንቀሳቃሽ ምስል ለአዘጋጀው አቢሲኒያ ቴሌቪዥን እናመሰግናለን

ታላቅ የግሪል ፓርቲ!

https://www.facebook.com/gukassa/videos/2208243325858231/
አዘጋጅ:- የ ኢትዮበርሊን የስፖርት ና የ ባህል ንኡስ ኮሚቴ
ቦታ:- ቴምፕል ሆፍ መናፈሻ
(Erholungspark Flughafen Tempelhof)

መግቢያ:- ኮሎምቢያ ዳም
(Eingang Kolombiadamm)
ቀን:- Juli 07.07.2018
ሰአት :- ከ 14:00 ጀምሮ

Ethiopberlin e.V. Grillparty 2018

እ.አ.አ በ16.06.2018 ቴፕልሆፍ ተበሎ በሚታወቀው የድሮ የ አየር ማረፊያ መናፈሻ ቦታ ላይ በ ኢትዮበርሊን ደማቅ የግሪል ፓርቲ ተደረገ፡፡ ይህ የግሪል ፓርቲ የተዘጋጀው የ ስፖርት ኮሚቴ በቅርቡ በጀርመን አገር ሽቱት ጋርት ከተማ በሚደረገው የ አውሮፓ የስፖርትና የ ባህል ዝግጅት ላይ ለመገኘት እንዲያስችለው እርዳታ ለመሰብሰብ እረድቶታል፡፡ ይህ የግሪል ፓርቲ አስደሳችና ኢየትዮጲያዊነት ደምቆ የዋለበት ቀን ነው፡፡ የ ኢትዮበርሊን መሀበር ወደፊትም ተመሳሳይ ዝግጅት ለማደረግ ይጥራል፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ድህረ ገጻችንን ለምትጎበኙ መቼ ና የት እንደምንዘጋጅ እዚሁ ላይ ሰለምንለጠፍ ደህረ ገጹን እንዲጎበኙ እንጋብዛለን!

Andargachew Tsige pardoned by Ethiopia

Attorney general says decision for Andargachew Tsige’s pardon was part of moves intended to ‘widen political space’.

Ethiopia has pardoned an opposition leader with British citizenship who had been sentenced to death.

Andargachew Tsige was found guilty of “terrorism” and sentenced in absentia in 2009 over his role in the opposition group Ginbot 7. He was the organisation’s secretary-general.

The father of three was arrested during a stopover at a Yemen airport in June 2014 and taken to Ethiopia.

Berhanu Tsegaye, Ethiopia’s attorney general, said on Saturday that Andargachew was pardoned “under special circumstances” along with 575 other inmates.

The decisions were made with the “intention of widening political space,” the attorney general told reporters in the capital, Addis Ababa.

Thousands of people including several senior opposition leaders have been freed since January [File: Reuters]

SOURCE: AL JAZEERA AND NEWS AGENCIES

A British national who was kidnapped and imprisoned in Ethiopia has been released from death row.

Theresa May thanks Ethiopia for release of Briton from death row.

Prime Minister Theresa May has thanked her Ethiopian counterpart for the release of Ethiopia-born Andargachew Tsege, as well as other prisoners, during telephone talks covering a range of issues.

Mr Tsege was accused by the Ethiopian authorities of being a terrorist and was tried with others in his absence in 2009 before being sentenced to death.

The father-of-three, who fled Ethiopia in the 1970s and sought asylum in the UK in 1979, had been a prominent critic of the country’s ruling party.

In June 2014 Mr Tsege, who is in his 60s, was kidnapped in Yemen and rendered to the African country, where he has since been held in prison.

A spokesman for Mrs May said she had congratulated her Ethiopian counterpart on his appointment and said the UK “firmly supported his reform and reconciliation efforts”.

The spokesman added: “The Prime Minister thanked Prime Minister Ahmed for the release of prisoners including British national Andargachew Tsege.

“They discussed the importance of development assistance, including the support the UK provides to bolster education, economic reform, industrialisation, anti-corruption and job creation in Ethiopia.

“They also discussed how the two countries could deepen their trade links, and touched on how the UK’s expertise in infrastructure and financing could support Ethiopia’s economic development agenda.”

Source: Evening Standard

 

ADWA-CELEBRATION  IN BERLIN

Ethio-Berlin e.V. – der Äthiopische Kultur-, Sozial- und Sportverein.

                                                ኢትዮ- በርሊን የባህል፣ሶሻልና ስፖርት ማሕበር ነው

-ማሕበሩ ዘረኛነትን፤ የብሔር፤የሃይማኖት ልዩነትንና የጾታ ጥላቻን ወዘተ አጥብቆ ይቃወማል።
– ለጀርመኖችና በበርሊን ከተማ ኗሪ ለሆኑ የሌላ አገር ዜጎች የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ አስመልክቶ ምሽቶችን ያዘጋጃል።
– ኢትዮጵያውያን የኪነ-ጥበብ ሰዎችን መደገፍ፤ ቢቻል ፕሮጄክት በመንደፍ ማገዝ
-ለልጆች፣ወጣቶችና ሴቶች የሚስማሙ እንቅስቃሴዎች፣ተግባሮችና ፕሮጄከቶች መደገፍ
-ምንም እነኩዋን የማህበሩ አባል ባይሆኑም ማህበራችን ለሕዝብ የሚያቀርባቸው ዝግጀቶች ላይ ተሳታፊ ለመሆን የሚፈልጉ ካሉ
 በሩ ክፍት ነው። አባል ላልሆነም ጭምር።

The Battle of Adwa was fought on 2 March 1896 between the Ethiopian Empire and the Kingdom of Italy near the town of Adwa, Ethiopia. This climactic battle of the First Italo-Ethiopian War, was a decisive defeat for Italy and secured Ethiopian sovereignty. As the 20th century approached, Africa had been carved …

2 comments on Home

 1. of course like your web-site but you need to check the spelling on several of your posts.
  Many of them are rife with spelling issues and
  I find it very troublesome to inform the reality nevertheless I’ll surely
  come back again.

  Look into my blog … Larue

Schreibe einen Kommentar

Deine E-Mail-Adresse wird nicht veröffentlicht. Erforderliche Felder sind mit * markiert.