Monat: März 2020

የኮሮና ቫይረስ በተመለከተ ከዶክተር ጸጋዮ ደግነህ

ለተከበራቹህ ወገኖች የኮሮና ቫይረስ በተመለከት ከጀርመን ያለውን ቴከኒካዊ ልምድና አስተያየት በማማከል ይጠቅማል ያልኩትን፣ ከዚህ በፊት ከተነበበው ወይም ክሚታወቀው በተጨማሪ ለማገናዘቢያ ይሆናል በማለትና በማሰባስብ እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራልሁ። ኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ ስጋቶችም እየጨመሩ ይገኛሉ። መደናገጥ፣ ፍርሃት እና ያለቅጥ መረበሽ ባያስፈልግም። አውሮፓ ውስጥ መንግስት አስፈላጊውን ቁጥጥሮች እና እርምጃዎችን ጀምሮዋል፣ መስሪያ ቤቶች፣ ተቋማት እና ኩባኛዎችም የመከላከያ እቅድ እያወጡ ነው። […]