Sport

ናሩድ ባዘጋጀው የ 2018 Interkulturelles Fussballturnier ባዘጋጀው የ እግር ኳስ ግጥሚያ ላይ የ ኢትዮበርሊን የ ስፖርት ቡድን ተጋብዞ ተሳትፏል፡፡

Ethioberlin e.V.

በዚህም ቀን የ ኢትዮበርሊን ሴቶች ዛሬም እንደተለመደው በግሩም ሆኔታ የባህል ቡና በማዘጋጀት አኩሪ ባህላችንን አሳይተዋል

  • Ethioberlin e.V.

ETHIO-BERLIN FUSSBALL MANSCHAFT: GEGRÜNDET NOVEMBER 2014, MITGLIEDER: 45

በ 2018 የ አውሮፓ የስፖርት ና የበህል በተደረገው ዝግጅት የኢትዮበርሊን ታደጊ የግርኳስ ቡድን እና የኢትዮበርሊን የግርኳስ ቡድን  እና ደጋፊዎቻቸው!!!

የኢትዮ-በርሊን የእግር ኳስ ቡድን አመሰራረት

የኢትዮ–በርሊን የእግር ኳስ ቡድን በ October 2014 ከ10 በማንበልጥ የማህበሩ ዓባላት ወጣት መሳይ ሽማግሌዎች ( ወ መ ሽ ) እግር ለማፍታታት ፣ ደም ለማዘዋወር ፣ በየአስሩ ደቂቃ እያረፍን በማህበራዊ ጉዳይ ላይ በመወያየት እንደዋዛ
በ Schillerpark በየሳምንቱ እዑድ ቀጭን ልምምድ በማድረግ ተጀመረ ።

በፎቶግራፍ ማስረጃነት እንደምናስተውለው ወቅቱ ብርዳማ ስለነበረ የእጅ ጓንት ፣ ወፍራም ሹራብና ካፖርት ፣ የራስ ቅል ቆብና ኮፍያ በመድፋት ፣ የአዘቦት ልብስ ለብሰን የስፖርት ጫማ በመጫማት ነበር መጫወት የጀመርነው ።
ውሎ አድሮ ! ጊዜው ብዙ ከኢትዮዽያና ኤርትራ በስደት ወደ ጀርመን የገቡበት ጊዜ ስለነበር የኛን የኳስ ልምምድ ፣ መውተርተር የሰሙ ወጣቶች በብዛት ተቀላቀሉን ።
በዚህም ሂደት ቁጥራችን ከ4 ቡድን በለይ በሚወጣው ቁጥር እያሻቀበ መሄዱን በተረዱት
” ወመሾች ” ምክክር ጉዳዩ ለኢትዮ– በርሊን ማህበር ቀረበ።
ማህበሩም በሰፊው ከተወያየበት በኋላ
1— አዲስ የመጡትን ወገኖቻችን እዚህ ከቆየነው ጋር ለመቀራረብ አንደሚረዳ:
2– ልጆችንና ወጣቶችን በማገናኘት በአካልና መንፈስ ከማጎልበት ባሻገር የሃገራቸውን ባህል ቋንቋና ልማድ ለማስተዋወቅና ለማጠናከር እንደሚያመች አምኖበት:
ገንዘብ ከዓባሎቹ በማሰባሰብና ከማህበሩ በመመደብ አስፈላጊ የስፖርት ቁሳቁሶችን ገዝቶ ፣ አሰልጣኝ መድቦ
ኢትዮ—በርሊን የስፖርት ክለብ ብሎ ቡድኑን በመሰየም ስራውን ተያያዘው ።

በመቀጠልም በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ዓባልነት ተመዝግበን በየዓመቱ በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ ለመሆን በቃን ።

በሂደቱም የኢትዮ—በርሊን የእግር ኳስ ቡድን:
2015 ፍራንክፈርት በተከናወነው የኢትዮ–አውሮፓ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ የኢትዮ—በርሊን ቡድን ለመጀመርያ ጊዜ ተሳትፎ በውጤቱ በተለይም ሜዳው ላይ ባሳየው ስፖርታዊ የወንድማማችነት ፣ ፍቅር አዘል የማህበራዊ እንቅስቃሴ በሌሎች ብዙሃን የቡድን ዓባላት ዘንድ አድናቆትን ከማስገኘት አልፎ ጥሩ ምሳሌ ለመሆን አብቅቶታል ።

በ2016 ሙኒክ ላይ በተካሄደው የኢትዮ–ጀርመን ካፕ ላይ 25 ተጫዋቾችን ይዞ በመሳተፍ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሶ የጠባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል ።

በዚሁ በ 2016 ባለንበት ከተማ ውስጥ ለአውሮፓው ግጥሚያ ዝግጅት እንዲሆን በማሰብ ከተለያዩ በከተማው ከሚገኙ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ ተካሂዷል ።
በተለይ NARUD ከሚባል 32 የተለያዩ ቡድኖች የተሳተፋበት የአፍሪካውያን የስፓርት ፌስቲቫል ላይ ያሳየነው ተሳትፎ በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ዕውቅናን እትርፎልናል ።
በተለይ ከጥቂት ቀናት በፊት በዚሁ ፌስቲቫል ላይ እንዲሳተፉ በማሰብ ብቻ አራት አምስት የማህበሩ ዓባሎች ተመካክረው በትጋትና ጥንካሬ በብድር ማሊያ ገዝተው ፣ አሰልጣኝ ከትልልቆቹ ተጫዋቾች መድበው የህፃናት ቡድን በማቋቋም ለቱርኔው አብቅተዋል :
እነዚህ ልጆች በጊዜው ያስገኙልን ከፍተኛ ዉጤትና አድናቆት ብቻ ሳይሆን በመቀጠልም ሌላ የጎልማሳ ቡድን በመጨመር በማህበሩ ሙሉ ኃላፊነት ዴንሃግ ላይ ሁለተኛ ! ሁለተኛ ! በመውጣት አሁንም ድረስ የሚያኮራን የታዳጊ ቡድን ለመሆን በቅተዋል ።

ለዚህም መሆን ጉልበታችሁን ፣ ጊዜ ፣ ገንዘባቸውን ሁሉ በመሰዋት ላገዛችሁ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና ይድረሳቸው ።

ከላይ በተጠቀሱትም ክንውኖች የማህበሩ ዓባሎች፣ ኢትዮጵያን የበርሊን ነዋሪወችና ወዳጆቻችን ደስተኛነታቸውን በመግለፅ ዕርዳታና ትብብራቸውን እስካሁን አላቋረጡብንም ።
ለዚህም ጭምር ምስጋናችን የላቀ ነው ።

የኢትዮ–ጀርመን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን የበለጠ ተጠናክሮና ተደራጅቶ በህጋዊነት ተመዝግቦ እንዲሰራ ክለባችን በሁለቱ የማህበሩ ተወካዮቹ ዓማካይነት ከፍተኛ እገዛና ግፊት አድርጎ ከሌሎች ዘጠኝ በጀርመን ከሚገኙ መስራች የኢትዮጵያን ክለቦች ጋር በመሆን በ März 2017 በቴሌኮንፈረንስ ፎርማል የጀርመን ስፖርት ፌዴሬሽን አቋቁመን በድጋሚ September 23. 2017 Nürnberg ላይ በግንባር ተገናኝተን ኮለንን መቀመጫው በማድረግ አዲስ ዓመራር መርጠን ፌዴሬሽኑን በማቋቋም ታሪክ ሰርተናል ።

ከዛ ቀደም ብሎ የ2017 ቱን ዓመታዊ ስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጅነት ለኢትዮ—በርሊን በመሰጠቱ ኢትዮ በርሊን ለመጀመሪያ ጊዜ እስካሁን በአንድ ቀን ይደረግ የነበረውን ፌስቲቫል ሁለት ቀን በማድረግ ፣ ተካፋይ ቡድኖችን ወደ 12 ከፍ በማድረግ ፣ የክብር እንግዳ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን በመጋበዝ የህፃናትና የባህል ፕሮግራም ሜዳ ላይ በማዘጋጀት ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈልንና የሜዲያ ትኩረት ያስከተለልንን
የኢትዮ-በርሊን ስፖርት ፌስቲቫል Juni 3/4 2017 ተግባራዊ በማድረግ እነሆ ለሌሎች ዓርአያ በመሆን ለኩራት በቅተናል ።

ኢትዮ- በርሊን ስፖርቱን በሚመለከት ስራችንን ባካባቢአችንና በጀርመኑ ፌዴሬሽን ብቻ ተወስነን አልቀረንም:
በአውሮፓ የኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ዓባል እንደመሆናችን ፌዴሬሽኑ ላለፉት ዓመታት ተዘፍቆበት የነበረውን የስነምግባር ፣ የፋይናንስ ፣ የድርጅትና የዓመራር ችግር በሚመለከት ተወካዮቻችን ከሌሎች የቦርድ ዓባሎች ጋር በመሆን ቀደም ብሎ በደብዳቤ ፣ በቴሌኮንፈረንስ ፣ በግንባር በመገናኘት ፣ በሜድያና በመጨረሻም Oktober 14, 2017 Amsterdam ( Holland ) ላይ በመገኘት መፍትሄ ይሆናል ብለው ያሰቡትን ሐሳብ በማቅረብና በማዋቀር ፌዴሬሽኑን አሁን ያለበት የተሻለ ደረጃ ላይ በመተባበር በጋራ ማድረስ ችለዋል ።
በመጨረሻም ቡድናችን በ2018 እንደተለመደው ባካባቢአችን ከሚገኙ ቡድኖች ጋር የሚያደርገው ግጥሚያ እንደተጠበቀ ሆኖ መጭው ፊንግስተን 19/20. 05.2018 ለሁለት ቀን ፍራንክፈርት ላይ የሚካሄደው የኢትዮ-ጅርመን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ
እንዲሁም Juni ውስጥ በርሊን በሚካሄደው የ NARUD አፍሪካ ስፖርት ፌስቲቫልና እንደተለመደው በ Juli ወር Stuttgart ላይ የሚከበረው በአውሮፓ የኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ፌስቲቫል ላይ ዋና ቡድኑንና የልጆች ቡድን ይዞ ለመካፈል በዝግጅት ላይ ይገኛል ።

ስለዚህ ውድ የኢትዮ–በርሊን ቡድን ፣ አባላቶችና ደጋፊወቻችን እንደተለመደው ትብብራችሁና ወደር የማይገኝለት ድጋፋችሁ እንዳይለየን ከወዲሁ እናሳስባለን ።

ከምስጋና ጋር !
የኢትዮ – በርሊን ስፖርት ክለብ